You are here

በቀጥታ ዘር መዝራት ዘዴ፡ ለደን ልማት እና ለተራቆተ መሬት መልሶ ማቋቋም

ቀጥታ ዘር መዝራት ዘዴ በደን ልማት ዘርፍ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ያመጣ ሲሆን፣ በተለይም በሰፊ መጠን ለሚተገበሩ የመሬት ማገገም ተግባራት ላይ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ ዘዴ ሆኖ ይታያል። 

ይህ ዘዴ የመሬት መራቆትና የአየር ንብረት ለዉጥ እየጨመረ በሚሄድበት ወቅት፣ ውስን ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም የስነ-ምህዳር አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ሁኔታ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ለማረጋገጥ ተግባራዊ አቀራረብን ያሳያል። 

ይህ መመሪያ ለብዙ ዓመታት የተሰበሰበ የተግባር ልምድና ሳይንሳዊ ምርምርን በመመርኮዝ፣ ለኤክስቴንሽን ወኪሎች፣ ለደን ልማት ባለሙያዎች አጠቃላይና የተደራጀ መመሪያ ይሰጣል። በውስጡ የተካተቱ የደረጃ በደረጃ ሂደቶች ጤናማና ለዉጥን ተቆቁመዉ የሚቆዩ ደኖችን ለማስፋፋት የተነደፉ ሲሆኑ፣ በዚሁ ዘዴ በመጠቀም ሀብት በተሻለ ሁኔታ መጠቀምና አሉታዊ አካባቢያዊ ተፅእኖን መቀነስ ያስችላሉ። 

በዚህ ተግባራዊ መመሪያ ላይ የቀረቡት ዘዴዎች በተለይ ሀብታቸዉ ውስን ለሆኑ አነስተኛ አርሶ አደሮችና ህብረተሰብን መሠረት አድርገዉ በሚተገበሩ የመሬት ማገገሚያ ፕሮጀክቶች ይበልጥ ተሰማሚ ናቸው። ቀጥታ ዘር መዝራትን በመተግበር፣ አሁን ያለዉንና ወደፊት ሊከሰት የሚችለዉን የአካባቢያዊ ችግሮችን ተቋቁመዉ ሊቆዩ የሚችሉ የመሬት አጠቃቀሞችን እና የመሬት መልሶ ማቋቋም ጥረቶችን ማጠናከር ይቻላል።

በቀጥታ ዘር መዝራት ዘዴ፡ ለደን ልማት እና ለተራቆተ መሬት መልሶ ማቋቋም | Forestry - Digital Forestry Information Hub (DFIH)