You are here

የዘላቂ ደን አስተዳደር

ሀገራችን ኢትዮጵያ በመልከዓ-ምድራዊ አቀማመጧ፣ የመሬት አቀማመጧና የመሬቷ ቅርጽ፣ አየር ንብረቷ፣ የዕፅዋት ሽፋኗ፣ የእንስሳት ዓይነቷ፣ የአፈር ዓይነቷ እና ባህሏ ከፍተኛ ተለያይነት (diversity) ያላት ሀገር ናት፡፡ ይህ የመልከዓ-ምድሯ አቀማመጥ፣ የመሬት አቀማመጧና የመሬቷ ቅርጽ፣ የአየር ንብረቷ እና የአፈር ዓይነቷ ተለያይነት ሀገራችንን ከፍተኛ የሆነ የዕፅዋት ዝርያ ክምችት እንዲኖራት አድርጓል፡፡ 

በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ባለው ማስረጃ 17 የግብርና የአየር ንብረት ቀጠና (Agro-climatic zone) እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለው መረጃ ደግሞ ሀገራችን 18 የግብርና የአየር ንብረት ቀጠና ያላት መሆኑን ያመለክታል፡፡ 12 ይህም ኢትዮጵያ እንደ አንዳንድ ሀገራት ልሙጥ ወይም ተመሳሳይ የተፈጥሮ ሀብት (የአየር ንብረት፣ የአፈር ዓይነት፣ ዕፅዋት፣ እንስሳት፣ ወዘተ) ያላት ሳይሆን ከፍተኛ ተለያይነት ያለው የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሀገር ናት፡ ፡ 

ይህም በቀላል ቋንቋ ሀገራችን ልዩ ልዩ የሰብል ዓይነት፣ የደን ዕፅዋት፣ የእንስሳት ሃብት እንዲኖራት፣ እንድታለማ እና እንድትጠቀም ረድቷታል፡፡

 

Sustainable Forest Management (SFM)- የዘላቂ ደን አስተዳደር ምንነት እና አስፈላጊነት | Forestry - Digital Forestry Information Hub (DFIH)

 

Contact Us

T (251) 115 52 28 88
Email: cccethiopia2@gmail.com 

Consortium for Climate Change Ethiopia
Yeka Sub City, On the way from Kazanchis to Abuare, Woreda 06, House No. 150
Addis Ababa, Ethiopia

Monday to Friday: 9am to 5pm
Saturday and Sunday: Closed